የግዛቱ የደን ጠባቂ እንደመሆኖ፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አስርት አመታት ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ 400,000 ዱናም የተፈጥሮ እንጨት ተክሎ እና ሌላ 400,000 ዱናም የግጦሽ መሬትን ይንከባከባል።
ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ ለእያንዳንዱ ደን የሚያዘጋጀው ማስተር ፕላን የደንን ሁኔታ የሚወስን እና ለነባር እና ለወደፊቱ ደኖች በሕግ የተጠበቀ ጥበቃ ያደርጋል።
ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ ለደን አስተዳደር ያለውን አመለካከት እየቀየረ ነው። እንደ ስያሜው እዚያ የሚበቅሉትን ዛፎች ላይ ሳይሆን መሬቱን ለማስተዳደር እንዲሁም በደኑ ሕይወት ውስጥ ያለው ጣልቃ ገብነት በተቻለ መጠን ትንሽ ማድረግ ነው። ለምሳሌ የተቃጠለን ደን ለመተካት ዛፎችን ለመትከል አይቸኩልም። ነገር ግን በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ እድሳት አቅም ይመረምራል። በኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ የተተከሉ ፈር ቀዳጅ ደኖች ቀስ በቀስ ለአዲሱ ትውልድ ደን ቦታ እየለቀቁ ነው። የእስራኤል የወደፊት ደን በሳይንሳዊ ምርምር ላይ የተመሰረተ፣ ለአካባቢያቸው ተስማሚ በሆኑ እጅግ በጣም ጥሩ የእፅዋት ምንጮች ዛፎች ላይ እና የደኑን አላማ በሚስማማ ክትትል እና አያያዝ ላይ የተመሰረተ ምርት ይሆናል።
ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ የንቦች ግጦሽ ሆነው የሚያገለግሉ እና የጋዛ ኤንቬሎፕ ሰፈሮችን በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ከጠላት አይን የሚደብቁ የአበባ ማር ዛፎችን ይተክላል።
የ የአበባ ማር ዛፎችን የበረሃ ደኖች ልዩ አረንጓዴ ቀለም ያበረክታሉ።
ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ በተሳሳተ እርሻ፥ ከመጠን በላይ መጠቀም እና በአየር ንብረት ለውጥ ለም መሬቶችን ወደ ማይጠቅሙ መሪትነት የሚቀይረውን የበረሃማነትን አጥፊ ሂደት ለመከላከል ልዩ የሆነ ቅርጠኝነት አለው። ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ ሂደቱን በመቀልበስ እና የማምረት አቅሙ ትንሽ የሆነ መሬትን ለምነት በመጨመር ለሰው እና ለተፈጥሮ ብዙ ጥቅም ሊሰጥ የሚችል ልምድ አከማችቷል።
የአየር ንብረት ለውጥ በመላው ዓለም የእሳት ቃጠሎዎች ቁጥር እና መጠን መጨመርን ያስከትላል። በእግረኞች ግድየለሽነትም ሆነ ዛፎችን በማቃጠል በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ እሳቶች በኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ ደኖች ውስጥ ይከሰታሉ። ነገር ግን በኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ ማስጠንቀቂያ እና የእሳት ማጥፊያ ስርዓት እሳቱ ብዙ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ስለሚጠፋ ማሕበረሰቡ ስለ ደን ቃጠሎ አይሰማም።
ይህ የዕሳት ማጥፋት ስርዓት የመመልከቻ ማማዎች እና በደን መንገዶች ላይ ከፍተኛ የመንቀሳቀስ ችሎታ ያላቸውና ቀልጣፋ የሆኑ የያሪት የደን-እሳት አደጋ መከላከያ መኪናዎችን ያጠቃልላል። ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ በእሳት የተጎዱ ደኖችን መልሶ የማቋቋም አቀራረቡን አዘምኗል። በዚሁም መሰረት በዋናነት በሥነ-ምህዳር የተፈጥሮ እድሳት ሂደቶች ላይ የተመሰረተ ነው።