ሻርሸርት ፓርክ፣ ናሃል ግራር "አረንጓዴ ደሴት" ሲሆን በምእራብ ኔጌቭ ለም የሆነ አፈራማ ሜዳ የሚገኝ ደን ነው። ደኑ የተተከለው ከናሃል ሃበሶር ገባር ወንዞች አንዱ በሆነው በናሃል ግራር በሁለቱም ዳርቻዎች ላይ ነው። ይህ የወንዙ ክፍል በዓመቱ ውስጥ በአብዛኛዎቹ ወራት ውስጥ ብዙ ውሃ ስለሚይዝ በአካባቢው ላሉ እንስሳት ጠቃሚ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ በደኑ ውስጥ ውብ መንገዶችን እና የብስክሌት መንገዶችን ምልክት በማድረግ በመዝናኛ ቦታዎች ውስትም የመጠጥ ውሃ እና በተሽከርካሪ ወንበር ተደራሽ የሚሆኑ ጠረጴዛዎች አዘጋጅቷል። የቴል ሀሮር ታሪካዊ ቦታ ከወንዙ በስተሰሜን በኩል የሚገኝ ሲሆን በዙሪያው ያለው ማራኪ የሆነ ዕይታ ከዋናው አናት ላይ በመሆን ማየት ይቻላል። ይህም ቦታውን ለመጎብኘት ለሚመጡ ሰዎች ተጨማሪ ደስታን ይሰጣል ።