በኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ውስጥ የደኑ ሚስጥር ይታወቃል።
መጀመሪያ ስንጀምር ግባችን እስራኤልን አረንጓዴ ማድረግ ነበር፣ እናም በፍጥነት ማደግ የሚችሉ ትላልቅ ዛፎችን በሰፊ ቦታ ላይ ተከልን። ለብዙ አመታት፣ ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ በእስራኤል ውስጥ ከተተከሉ የጥድ ደኖች ጋር ይያያዝ ነበር።
የብዝሃ ህይወት አስፈላጊነት ግንዛቤ እያደገ ሲሄድ የደን ልማት አቀራረባችንም ተለወጠ። የዛሬዎቹ ደኖች ከጥንቶቹ ጋር አይመሳሰሉም - የተለያዩ እና ክፍት ናቸው ፣ለተለያዩ እፅዋት እና እንስሳትም የመኖሪያ ስፍራን ይሰጣሉ ፣ በተጨማሪም ለሁሉም አይነት ሰዎች ድንቅ መዝናኛ ሆነው ያገለግላሉ።