የዴቪድ ናህሚያስ ማዐከል ከኦፋኪም ብዙም ሳይርቅ በሚገኘው የጊላት ጊቢ ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ውስጥ ይገኛል
ይህ ታሪካዊ ጊቢ በ53 ሄክታር መሬት ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኝ ሲሆን ከበፊቱ የእስራኤል ግዛት ጀምሮ ክፍት የነበረ ስፍራ ነው። ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ለጫካው ውበት የሚሆኑና ደን ለማልማት የሚፈለጉ ዛፎችን የሚያቀቀርበውን ጊላት የተክሎች ማሳደጊያንም ያስተዳድራል። የጎብኝዎች መቀበያ ማዕከላት የሚመጡትን ጎብኝዎች በኔጌቭ ውስጥ የሚሰሩትን ስራዎች ያስተዋውቋቸዋል ። የማዕከሉን አጠገብ ተከትሎ የሚሄድ በዛፍ ተከልሎ የጫካውን ዱካ ተከትሎ የሚሄድ ለአካል ጉዳተኞች በቀላሉ እንዲመች ተደርጎ የተሰራ የሽርሽር መንገድ አለ ።
ሌሎች በጊቢው ውስጥ ከሚገኙት ነገሮች መካከል እየጠፉ ያሉ ፍራፍሬ ሰጪ ዛፎች የተዘጋጀ የአትክልት ስፍራ ፣ ታሪካዊ የሆነ የአጋቫ ተክል ቃጫ የሚመረትበት የነበረ የስራ ክፍል ፣ እንዲሁም የሙከራ የጆጆቫ ግሮቭ ይገኙበታል።
የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የደቡብ ክልል ቢሮዎችም በጊላት ጊቢ ውስጥ ይገኛል።
በጊላት ማዐከል ውስጥ የተጠናቀረ ጉብኝት የተክል ማሳደጊያውንና ሙሉ ማዐከሉን ጨምሮ ወደ አራት ሰአት ይፈጃል።
ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያለበት ቦታ ሰለሆነ የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ አስጎብኝ ጉዞውን እየመራ ይሄዳል ።
የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ አስተርጓሚ ቡድንም ወደጊላት ያለውን ጉብኝት ከሌሎች የተለያዮ ሀሳቦች ጋር በማደባለቅ ማራኪ ያደርጉታል ።