የሴግቭ ጫካ ወደ10,000 የሚጠጋ በምእራባዊው ጋሊሌ ያለ ቦታ ይሸፍናል ። ለመኪና ትእይንት የሚመቸው ከፍታ ያለው መንገድ ጫካውን እያቋረጠ አሽከርካሪውን አኮ ሸለቆ እና አካባቢው ላየይ ያለውን የመሬት ገፅታ ያሳያል ። በምዕራባዊው መንገድ መጨረሻ ኬኬኤል- ጄኤንኤፍ ለመዝናኛነትና ለሽርሽር የሚሆን የሴግቭ መዝናኛ ቦታ ተዘጋጅቷል ።