መንደግስቱ ከተመሠረተ በኋላ፣ ከሬን ካየመት ለእስራኤል አይሁድ ካልሆኑ ባለቤቶች የወሰደው መሬት መጠን እየቀነሰ፣ መሬቱን ከጥፋት የማዳኑ መጠን ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። መንግስቱ በእስራኤል ውስጥ የአብዛኛው መሬት ባለቤት ሆኗል፣ስለሆነም መንግስት እነዚህን ቦታወች ያስተዳድራል እና ያለማል።
የእስራኤል መንግስት እና ከረን ካየመት ለእስራኤል በተለያዩ ኤጀንሲዎች መሬቶቻቸውን በማስተዳደሩ ምክንያት የተፈጠረውን ተመሳሳይ ስራ ለማቆም፣ የነዚህን መሬቶች አስተዳደር፣ ጥበቃ እና እንክብካቤ በመንግስት እጅ ለማሰባሰብ እና የእስራኤል ምድርን ከጥፋት ለማዳን የከረን ካየመትን ስልጣን ለማጠናከር ወስነዋል።
ስለዚህ የዚህ ስምምነት ተዋዋይ ወገኖች በሚከተለው መልኩ ተስማምተዋል፡-
- የመሠረታዊ እስራኤል መሬት ሕግ ሥራ ላይ ሲውል፡ (ከዚህ በኋላ “ሕጉ” እየተባለ የሚጠራው)፣ የግዛት መሬት ወይም የልማት ባለሥልጣን ወይም የከረን ካየመት ለእስራኤል መሬት የሆኑ መሬቶች አስተዳደር ያለፈው ወይም ወደፊት የሚገዛው በመንግስት እጅ ውስጥ ይሰበሰባል
- መንግሥት “የእስራኤል የመሬት አስተዳደር” (ከዚህ በኋላ “አስተዳደሩ” እየተባለ የሚጠራ) ያቋቁማል እና ከከረን ካይመት ለእስራኤል ጋር በመመካከር የአስተዳደሩን ዋና ዳይሬክተር ይሾማል።
ዳይሬክተሩ የዚህን ቃል ኪዳን አፈፃፀም ከዚህ በኋላ "ሚኒስትሩ" ተብሎ ለሚጠራው በመንግስት ለተያዘው ሚኒስትር ተገዥ ይሆናል።
- በአንቀፅ 1 የተደነገገው ቢኖርም በመሬት መዝገብ ውስጥ በተመዘገቡት የመሬት ይዞታዎች ባለቤትነት ላይ ምንም አይነት ለውጥ አይኖርም, የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ ወገኖች በተለየ መሬቶች ላይ ለመመዝገብ ከተስማሙ በስተቀር ምንም አይነት ለውጥ አይኖር፤ የመንግስት ስም ወይም በከረን ላይሜት ሌእስራኤል ስም በመለዋወጥም ሆነ በሌላ መንገድ።
- የእስራኤል መሬቶች የሚተዳደሩት በህጉ መሰረት ነው ማለትም መሬት አይሸጥም በሚለው መርህ መሰረት ግን በሊዝ ብቻ የሚሰጥ እና በአንቀፅ 9 የተቋቋመው ቦርድ ባወጣው የመሬት ፖሊሲ መሰረት ነው። ቦርዱ የመሬት ያለውን የሰዎችን የማስተናገድ አቅም ለመጨመር እና በግለሰቦች እጅ ውስጥ ያሉ መሬቶችን ብዛት መቀነስን በማሰብ የመሬት ፖሊሲ ያወጣል። በተጨማሪ የከሬን ካየመት ለእስራኤል መሬቶች በከሬን ካየመት ሌእስራኤል መተዳደሪያ ደንብ እና መተዳደሪያ ደንብ ይተዳደራሉ።
- አስተዳደሩ የተወሰነ ግብይትን በሚመለከት በአንድ ወይም በሌላ ዝርዝር ሁኔታ በአንቀጽ 4 ከተጠቀሰው የመሬት ፖሊሲ መርሆዎች ማፈንገጥ አስፈላጊ እንደሆነ ካመነ፣ ግብይቱ የሚፈፀመው ከተፈቀደው ጋር ብቻ ነው። በአንቀጽ 9 የተቋቋመ ቦርድ እና በከሬን ካየመት ስም የተመዘገበ መሬት በከሬን ካየመት ለእስራኤል ፍቃድ ወይም የሌላ እስራኤል መሬት በሚመለከት በሚኒስትሩ ፈቃድ ነው።
- የእስራኤል መሬትን በሚመለከት ማንኛውም ግብይት በአስተዳደሩ የተመዘገበው የዚህ መሬት ባለቤት ወኪል ሆኖ የሚፈፀም ሲሆን ከእስራኤል መሬት የሚገኘው ማንኛውም ገቢ የተመዘገበው ባለቤት ነው። እና ግዛቱ ይህንን ቃል ኪዳን ግምት ውስጥ በማስገባት የአስተዳደር ወጪዎችን ለመሸከም ይቀበላል
- አስተዳደሩ ለተመዘገቡት የእስራኤል ባለቤቶች በየሦስት ወሩ አንድ ጊዜ (እና ሕጉ ከፀናበት ቀን ጀምሮ ስድስት ወር ሲያልቅ ለመጀመሪያ ጊዜ) የገቢውን እና የምድራቸውን አስተዳደር የወጪ ሪፖርት ያቀርባል። ወጪው በአስተዳደሩ የተወሰነ፥ የተወሰነ የገቢ መጠን በመቶኛ ወይም በመሬቱ የተወሰነ የመለኪያ አሃድ ላይ እንደ ኮታ ያካትታል። እንደዚህ አይነት ዘገባ ሲቀርብ፣ ማንኛውም ቀሪ ሂሳብ ለከሬን ካየመት ሌእስራኤል ክሬዲት የሚታየው ከሆነ ለመንግስት እንደ ዕዳ ተቆጥሮ በመንግስት የሚከፈል ሲሆን ፤ ለከረን ካየመት ሌእስራኤል ዴቢት የታየ ማንኛውም ቀሪ ሂሳብ ደግሞ ለከረን ካየመት ሌእስራኤል እንደ ዕዳ ይቆጠራል። ስለሆነም ለመንግስት የሚከፈል ይሆናል።
- አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ የእንቅስቃሴውን ሪፖርት ለመንግሥት እና ለከረን ካይመት ለእስራኤል ያቀርባል።
- መንግሥት የመሬት ፖሊሲን የሚያወጣ፣ የአስተዳደሩን የበጀት ፕሮፖዛል የሚያፀድቅና የአስተዳደሩን ተግባራት የሚቆጣጠር በሚኒስቴሩ ሰብሳቢነት የሚተዳደር ቦርድ ያቋቁማል። ቦርዱ ይህ ስምምነትተፈፃሚ የሚሆንበትን መንገድ የሚቆጣጠር ይሆናል። የቦርዱ አባላት ቁጥር አሥራ ሦስት; ከመካከላቸው ግማሹ፣ በአንድ ያነሰ፣ በከሬን ካየመት ለእስራኤል አቅራቢነት ይሾማል። የቦርዱ አባላት በተሾሙበት መንገድ ሊተኩ ይችላሉ። የቦርዱ ሹመትና የአባላቶቹ ስም በየጊዜው በተሰየመው ማስታወቂያ በሬሹሞት ታትሞ ይወጣል።
- የእስራኤል መሬቶችን መልሶ ማልማት እና ደን ልማት በከረን ካየመት ሌእስራኤላውያን ስራ ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም "የመሬት ልማት አስተዳደር" (ከዚህ በኋላ "የልማት አስተዳደር" ተብሎ ይጠራል) ያቋቁማል። ከረን ካየመት ሌእስራኤላውያን ከሚኒስትሩ ጋር ከተማከሩ በኋላ የልማት አስተዳደርን የሚመራ ዳይሬክተር ይሾማሉ፣ እሱም ለከረን ካየመት ለእስራኤል ተገዢ ይሆናል።
- የልማት አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ (ሕጉ በሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ወር ሲያልቅ) ለእስራኤል መሬት ልማትና ደን ልማት ዕቅድ አውጥቶ ለመንግስት እና ለከሬን ካየመት ለእስራኤል ያቀርናል። መርሃግብሩ ከግብርና ሚኒስትር ጋር በተሟላ ቅንጅት ይዘጋጃል።
- የግብርና ሚኒስቴር የደን ልማት ክፍል ከዚህ በኋላ በደን ልማት ላይ ብቻ መሳተፍ አለበት። ይሁን እንጂ የግብርና ሚኒስትሩ በ 1926 የደን ልማት አፈፃፀም ላይ በልማት አስተዳደር መሰረት ስራውን ያከናውናል።
- የልማት አስተዳደሩ የእስራኤል መሬቶችን መልሶ የማግኘት፣ የማልማት እና የደን ልማት ሥራዎችን በተመዘገቡት ባለቤቶች ወኪልነት ይሠራል። እና ኪረን ካይሙት የልማት አስተዳደርን አስተዳደራዊ ወጪዎች ለመሸፈን በዚህ ስምምነት መሰረት ተስማምቷል።
- የእስራኤል መሬቶችን መልሶ መያዝን፣ የማልማት እና የደን ልማት ሥራዎች ላይ የሚውለው ወጪ ሥራው በሚካሄድባቸው መሬቶች በተመዘገቡት ባለቤቶች ላይ ይወድቃል። ስለሆነም ልማት አስተዳደሩ በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ (እና ለመጀመሪያ ጊዜ 9 ወሩ ሲያልቅ ህጉ ከፀናበት ቀን ጀምሮ) ለተመዘገቡት የወጪ ባለቤቶች ቀደም ሲል ለመሬታቸው ያወጡትን ሪፖርት ያቀርባል።
ቀደም ሲል እንደተገለፀው ሪፖርቱ ሲቀርብ፣ የመንግስት ወይም የልማት ባለስልጣን ላይ ዕዳ የታየ ማንኛውም ቀሪ ሂሳብ ከነሱ የሚገባ እና ለከረን ካየመት ለእስራኤል የሚከፈል ዕዳ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግስት በከረን ካየመት ለእስራኤል ስም የተመዘገበውን መሬት የማስመለስ፣ የማልማት ወይም የደን ልማት ስራ እንዲያካሂድ ለልማት አስተዳደሩ ሲጠይቅ ኬረን ካየመት ሌእስራኤል ስራውን ከማከናወኑ በፊት ለመንግስት በጽሁፍ ያሳውቃል። በወጪው ማስፈጸም ያልቻለው መንግሥት ለሥራው የሚያስፈልገውን ወጪ ይሸከማል፣ መጠኑም ለከረን ካይመት በስጦታ፣ በብድር ወይም በንብረት መለዋወጥ ወይም በሌላ መንገድ እንዲከፈል በመንግስት እና በከሬን ካየመት ሌእስራኤል መካከል ስምምነት ሊደረግ ይችላል።
- ከከረን ካየመት ለእስራኤል ጋር የተሳሰረው የመሬት መስመለስ እና ልማት ቦርድ የልማት ፖሊሲውን በግብርና ሚኒስትሩ የግብርና ልማት ዕቅድ መሠረት ያስቀምጣል። ቦርዱ የልማት አስተዳደሩን የበጀት ፕሮፖዛል ያፀድቃል፣ የልማት አስተዳደሩን እንቅስቃሴ እና ይህን ስምምነት የሚፈፅምበትን መንገድ ይቆጣጠራል። የቦርዱ አባላት ቁጥር አሥራ ሦስት; ግማሹ፥ በአንድ ያነሰ፥ በመንግስት ይሾማል። የቦርዱ አባላት በተሾሙበት መንገድ ሊተኩ ይችላሉ። ቦርዱ የሚመራው በከረን ካየመት ሌእስራኤል የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወይም በከረን ካየመት ሌእስራኤል በተሾመ ሰው ነው።
- ከረን ካየመት ሌእስራኤል እንደ ዓለም አቀፍ የጽዮናውያን ድርጅት ራሱን የቻለ ኤጀንሲ ሲሆን በእስራኤል እና በዲያስፖራ ከሚኖሩ የአይሁድ ሕዝብ መካከል፣ መሬቱን ከጥፋት ለመቤዠት ገንዘብ በማሰባሰብ እና የመረጃ እና የጽዮናዊት-እስራኤል ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ መስራቱን ይቀጥላል። መንግስት በእስራኤል እና በውጪ ሀገር ውስጥ በመረጃ እና በፕሮፓጋንዳ እንቅስቃሴዎች ለከሬን ካየሜት ሌእስራኤል እርዳታ ይሰጣል።
- ይህ ስምምነት የሚፀናውም ሕጉ በወጣበት ቀን ሲሆን ለአምስት ዓመታትም ፀንቶ ይቆያል። የዚህ ቃል ኪዳን ተዋዋይ ወገኖች አንዱ፣ አምስቱ ዓመታት ከማለቁ ቢያንስ ስድስት ወራት በፊት፣ ውሉን ላለመታደስ ፍላጎት እንዳለው ካላሳወቀ በቀር፣ የስምምነቱ ጊዜ ወዲያውኑ ለአምስት ዓመታት ሊራዘም ይችላል። ስለዚህ ከአምስት ዓመት ጊዜ ወደ ሌላ አምስት ዓመት ጊዜ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ስምነቱ ይራዘማል።
- ሕጉ ከተሻረ ወይም ከተሻሻለ፣ ከረን ካየመት ሌእስራኤል ለመንግሥት በጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት ከዚህ ስምምነት መውጣት ይችላል። ነገር ግን መንግስት የመሻሪያውን ማሻሻያ አስቀድሞ በጽሁፍ ካሳወቀ እና ከረን ካየመት ሌእስራኤል ምንም ተቃዎሞ ካልገለፀ ኬረን ካየመት ሌእስራኤል ከዚህ ስምምነት መውጣት አይችልም።
- በአንቀጽ 17 ወይም በአንቀጽ 18 መሠረት ይህ ስምምነት ውድቅ ከሆነ ሕጉ ከመፈጸሙ በፊት ወዲያውኑ የነበረው አቋም ለመመለስ መንግሥት አስፈላጊውን ሕግ አካሄድ ለመወሰን ለእስራኤል ፓርላማ ያቀርባል።
- በዚህ ስምምነት ውስጥ ካሉት ተዋዋይ ወገኖች አንዱ መለወጥ እንዳለበት ካሰበ ለሌላኛው ወገን የጽሁፍ ማስታወቂያ መስጠት አለበት። እሱም ማስታወቂያው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለሐሳቡ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ምላሽ ይሰጣል። መልሱ አዎንታዊ ከሆነ, መልሱ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በቀረበው ሀሳብ መሰረት ስምምነቱ እንደተሻሻለ ይቆጠራል።
- ይህ ስምምነት ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ተዋዋይ ወገኖች ሁሉንም አስፈላጊ ነገር ሁሉ ያደርጋሉ። በተጨማሪም ሁሉም የስምምነት ጉዳዮች ለማክበር ይገደዳሉ።
ፊርማዎቻቸውን ያዘጋጁበት ምስክር
በእስራኤል መንግሥት ስም የገንዘብ ሚኒስትር ሚስተር ሌዊ ኤሽኮል
እና ከረን ካየመት ለእስራኤል በኩል፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ሚስተር ጃኮብ ትሱር፣
በኢየሩሳሌም፣ በ20ኛው የኪስሌቭ ቀን፣ 5722 (ኖቬምበር 28፣ 1961)።
ሌቪ ኢሽኮል
የገንዘብ ሚኒስትር
ያዕቆብ ቱር
የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር
ከረን ካየመት ለእስራኤል
የዚህ ትርጉም ጽሑፍ አስገዳጅ አይደለም፣ ብቸኛው ትክክለኛ ጽሑፍ የዕብራይስጥ ኦርጂናል ነው።