ደኖችን ከእሳት ለመከላከል ደኖችን መንከባከብ

2010 የቀርሜሎስ እሳት። (ፎቶ: ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፎቶ ማህደር)
በደን ውሰጥ የሚከሰቱ እሳቶች የዛፎች እና የደን ሥነ-ምህዳር ዋነኛ ጠላት ናቸው። የደን እሳት የሚቀጣጠለው ከፍተኛ ሙቀት፣ ኦክሲጅን እና ተቀጣጣይ ነገሮች በደን ውስጥ ሲኖሩ ነው። የደን ቃጠሎ የሚቀጣጠል ቁሳቁስ ሲታገዝ በአግድምም ሆነ ወደ ላይ ፣ በገደል እና በሸለቆዎቸ ውስጥ በአየር ሁኔታ ፣ በዋነኛነት ደግሞ በጠንካራ ንፋስ ፣ ዝቅተኛ እርጥበት እና ከፍተኛ የሙቀት መጠን ይሰራጫል።

የደን አርሶ አደሮች የደን ቃጠሎን በመከላከል እና በመቀነስ ረገድ ውጤታማ የመሆን አቅማቸው በዋናነት በአካባቢው ያለውን ተቀጣጣይ ነገሮች በመቀነስ እና የእሳቱን ወደ ላይ እና በአግድም እንቅስቃሴ በመገደብ ነው።

ጥሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች ለምሳሌ መንገድ እና የውሃ አቅርቦት፣ በደን ውስጥ የሚከሰት እሳት ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት ይረዳል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እሳቱን አስቀድሞ ማወቅ እና በቂ የእሳት አደጋ ተከላካዮች መኖራቸው የደን እሳትን ለመቀነስ ይረዳል።

ኬ ኬ ኤል - ጄ ኤን ኤፍ በዓመት ውስጥ በአማካኝ 600 በሚሆኑ ሰደድ እሳቶች ባደረሱት ጉዳት በ800 ሄክታር (2,000 ኤከር) ቦታ ላይ የሚገኙ 50,000 የተጎዱ ዛፎችን መልሶ አድሷል።

ኬ ኬ ኤል - ጄ ኤን ኤፍ የደን እሳት አስተዳደርን በሁለት ዋና ዋና ቦታዎች ይከፍላል።
  1. የእሳት አደጋን ለመከላከል የሚደረግ የደን እንክብካቤ
  2. የደን ቃጠሎ ጉዳትን ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎች
የደን ቃጠሎን ቁጥር የሚቀንሱ ተጨማሪ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የደን ቃጠሎን አስመልክቶ የማሕብረተሰብ ተሳትፎ በውይይት፥ በትምህርት ፣በህግ ፣በህግ አስከባሪ እና በቅጣት ማድረግ ይገኙበታል ።

የእሳት አደጋን ለመከላከል የሚደረግ የደን እንክብካቤ

የተለያዩ ዛፎች እና ቁጥቋጦዎች የተለያየ ደረጃ ተቀጣጣይነት እና የፍጆታ መጠን አላቸው።
ኬ ኬ ኤል - ጄ ኤን ኤፍ ተቀጣጣይነታቸው በአንጻራዊ ሁኔታ አነስተኛ የሆኑና እሳት አደጋን የሚቀንሱ የእጽዋት ዝርያዎች ይተክላል። ከ 1950 ዎቹ ጀምሮ የተደረጉ ጥናቶች የእሳት ቃጠሎን የሙቀት መጠን እና የደን ዛፎች እና ቁጥቋጦዎች የእሳት ፍጆታ መጠንን መርምረዋል። በጥናት ግኝቶቹ መሰረት ለብዙ አይነት ዛፎች እና ቁጥቋጦዎች የጥናቱን ዉጤት የሚያሳዩ ዝርዝር ሰንጠረዦች ተዘጋጅተዋል። ተጨማሪም የደን አተካከል እና አጎራባች መገናኛ ቦታዎችን በተመለከተ ምክረ-ሐሳቦች ተሰጥተዋል። የጥናቶቹ አላማ ዝቅተኛ ተቀጣጣይነት እና የፍጆታ ፍጥነትታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዛፎችን እና ቁጥቋጦዎችን መትከል፣ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ የእሳት ቃጠሎ እና ስርጭት እድልን መቀነስ እና በተለዩ የእሳት ማጥፊያ መስመሮች ላይ ዛፎችን መትከል ነበር ።

በእስራኤል የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው አቴል ታማሪስክ በሌላ ስሙ ሳልት ሴዳር በመባል የሚታወቀው የእሳት ቃጠሎን ለመከላከል በጣም ተስማሚ የሆነ ዛፍ ነው።
በተጨማሪም ዝቅተኛ ተቀጣጣይነት መጠን ያላቸው ሶስት ቁጥቋጦዎች - ካፐር, ማስቲካ እና ኦሊንደር ናቸው።

በተጨማሪም የሳይፕስ እና የሳልት ሴዳር ዛፎች እንዲሁም አነስተኛ ተቀጣጣይነት መጠን ያላቸው ቁጥቋጦዎች ደኖች ውስጥ ቢተከሉ እንደ እሳት መከላከያ እና እሳት እንዳይዛመት እንደሚያግዱ የሚያሳየውን በእስራኤል ውስጥ ደኖችን ለመትከል የተሰራውን ሞዴል ኬ ኬ ኤል ጄ ኤን ኤፍ ተግባራዊ አድርጓል።

የተተከሉ የችግኝ ረድፎች ድግግሞሽ እንደየአካባቢው ሁኔታ ይለያያል (ማጋደል ፣ ሰሜናዊ ወይም ደቡብ ተዳፋት ፣ የንፋስ አቀጣጫ እና የመሳሰሉት)። በሸንተረሮች እና ከፍታዎች ላይ የእሳት መከላከያዎችን ለመፍጠር የተራራቁ ዛፎች ዝቅተኛ እና የተንሰራፉ አጫጭር ቁጥቋጦዎች ጋር በትንሹ ይተከላሉ።
ፎቶ: ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፎቶ መዝገብ ቤት

የትንሽ እድሜ ደኖች እንክብካቤ

የደን ቃጠሎን ለመከላከል ኬ ኬ ኤል - ጄ ኤን ኤፍ በትንሽ እድሜ ደኖች እና የትልቅ እድሜ ደኖች መካከል ያለውን እንክብካቤን ይለያል። ትንሽ እድሜ ደን ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ የተተከለ እና ለእሳት በጣም የተጋለጠ ነው። እሳት ትንሽ እድሜ ያለው ደን ላይ ሙሉ በሙሉ ጉዳት ስለሚያደርስ የደኑን የተፈጥሮ እድሳትን ይገድባል። በትንሽ እድሜ ደን ውስጥ የእሳት ቃጠሎን ለመከላከል በዙሪያው ያለው ቦታ መለየት አለበት። በውስጡ ያለው ቦታ የእሳት መከላከያዎች ሊኖሩት ይገባል። የሚቀጣጠሉ ንጥረ ነገሮች መጠን በአካባቢው (ቀላል እና ከባድ ተቀጣጣይ ነገሮች) መቀነስ አለበት። በተጨማሪም የችግኝ እድገትን በመቆጣጠር፣ በመዝራት ፣ በግጦሽ እና በመሳሰሉትን ማድረግ ያስፈልጋል።.
የደን ውስጥ ግጦሽ የደን ቃጠሎ አደጋን ለመቀነስ አንዱ ዘዴ ነው። ምክንያቱም ግጦሽ ለእሳት ማገዶ ሆኖ የሚያገለግለውን ባዮማስን ክምችትን ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት የእሳት ቃጠሎ እንዳይነሳ እና እንዳይዛመት ይረዳል።

እሳት የሚጀምረው በትንሽ ባዮማስ ክምችት (ቅጠሎች ፣ ቅርንጫፎች ፣ ሳር) ነው። ወደ ዛፉ አናት ላይ መሰራጨታቸው በደንው ወለል እና በዛፉ አናት መካከል ባለው ተቀጣጣይ ንጥረ ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው። ትክክለኛ የግጦሽ እርባታ ባዮማስ ክምችት እና የዛፎቹን ቅርንጫፎች ከመሬት ላይ ያስወግዳል። ስለሆነም የእሳት ቃጠሎዎችን እና መጠናቸውን በእጅጉ ይቀንሳል. ቢያንስ የሶስት አመት እድሜ ያለው ትንሹ ደን በበልግ ወቅት በዛፎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ የግጦሽ መንጋውን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን ይህም በሄክታር ቢያንስ 1,000 ኪሎ ግራም ደረቅ ቁሳቁስ ባዮማስ ክምችት ይቀንሳል። ይህም በበጋ ወቅት የደን ቃጠሎ አደጋን ይቀንሳል።
በቤን ሸመን ደን ውስጥ የተቃጠለ ዛፍ። ፎቶ: ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፎቶ ማህደር
አካባቢን በመትከል እና ለግጦሽ የሚሆን ቦታን ክፍት ለማድረግ ሌላው ጉዳይ በፍጥነት የሚበቅሉ ዝርያዎች፣ በዋናነት ኮኒፈሮች እና ቀስ በቀስ በማደግ ላይ ያሉ ዝርያዎች በተለይም ብሮድሊፍ ድብልቅ መትከል ነው።
ያእድገት ፍጥነታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዝርያዎች ያሏቸው ደኖች ለግጦሽ ክፍት የሚሆኑበት ጊዜ የሚዘገይ ሲሆን ሚግጡት እንስሳት ወደ ደኑ የሚገቡበት ሁኔታ ቀድሞ የተዘጋጀ መሆን አለበት።
 
ደኖችን ከእሳት ለመከላከል ሌላኛው ስራ ባዮማስ ክምችትን በፀረ-ዓረም መድሀኒት መርጨት ነው። ይህ ስራ የሚረጨውን የኬሚካል አይነት፣ እንዴት እንደሚሰራ እና የተለያዩ ዛፎች ለሚረጨው ኬሚካል ያላቸውን ጥንካሬ በጥልቀት ማወቅን ይፈልጋል። የዚህ ስራ ውጤታማነት ኬሚካል የሚረጨው ድርጅት ያለው የዕውቀት ደረጃ ላይ መሰረት ያሚያደርግ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ትንሽ እድሜ ባላቸው ደኖችን በመትከል ወይም ለተፈጥሮ እድሳት በሚዘጋጅበት ጊዜ በደንው ዙሪያ ባለው ቦታ ላይ በደን የተሸፈነው ትንሽ ክፍል ማጠር አካባቢን እሳት ለመቆጣጠር ይጠቅማል።

ወጣት ዝግባዎች። ፎቶ: ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፎቶ ማህደር

በእድሜ የጎለመሱ ደኖችን መጠበቅ

በእድሜ የጎለመሱ የደን የዛፍ መገናኛ ላይ ለሚገኙ ዛፎች ዋና ስራዎች የንፅህና አጠባበቅ ፥ ቀጭን፥ መቁረጥ እና የዛፉን ቆሻሻ መቆራረጥን እና ማስወገድን ያካትታሉ። በደን መገናኛ ቦታዎች ውስጥ የሚቀጣጠሉ ነገሮችን መጠን ለመቀነስ ሊከናወኑ ከሚችሉ ተጨማሪ ስራዎች መካከል የእሳት መከላከያ እና የግጦሽ መስመሮችን መፍጠር እና መጠገን ይገኙበታል። የደን አጠባበቅ የደን መገናኛ ቦታዎች መርሃ ግብር ማዘጋጀትን ይጠይቃል። ይህም ስራ የደኑን አካላዊ ሁኔታ፥ የደኑን ክፍል ወይም ደኑ ያለበት ሁኔታ በዋነኝነት ደግሞ የደን ውስጥ የእሳት መነሻንና መስፋፋትን ስጋት ታሳቢ በማድረግ እንደ ቅደምተከተላቸው የሚወሰዱ ስራዎችን ያካትታል።

ይህ ሥራ ተጓዦችን እና ጎብኝዎችን የሚያገለግሉ ዋና መንገዶችን (ለምሳሌ በመዝናኛ ቦታዎች)፣ በዋና ሸንተረር መስመሮች እና በተለይም ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ደን ከመኖሪያ ማህበረሰቦች እና ሌሎች መገልገያዎች ጋር በሚገናኝበት መንገድ ላይ የእሳት መሰናክሎችን መፍጠርን ያካትታል።
 
በእድሜ የጎለመሱ ደኖች ላይ የሚደርሰውን የእሳት ጉዳት ለመቀነስ በኬ ኬ ኤል ጄ ኤን ኤፍ የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።

የንፅህና አጠባበቅ -
በደንው የህይወት ዑደት ውስጥ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እየተከናወነ ያለው ስራ ውስጥ የተተከሉም ሆኑ ለመድረቅ የተቃረቡ፥ የሞቱ / የደረቁ / የታመሙ ዛፎችን ከደን ውስጥ ማስወገድ ነው። በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሊወገዱ የማይችሉ ዛፎች 1 ሜትር ርዝመት ያላቸው ጉቶዎች እንዲሆኑ ተደርገው ይቆረጣሉ፤ እነሱም በዚያ ደን ክፍል ውስጥ ተበታትነው ይቀራሉ።

የተመረጡ ዛፎችን ማስወገድ - በሐሳብ ደረጃ, የተመረጡ ዛፎችን የማስወገድ ስራ በየሰባት እስከ አሥር ዓመታት ውስጥ መደረግ አለበት። ይህ ስራ ደግሞ ብዙም ያላደጉ ዛፎችን እና የደረቁ ዛፎችን ማስወገድን ይጠይቃል። በኮኒፈር ደኖች ውስጥ የተመረጡ ዛፎችን ማስወገድ የሚከናወነው የደኑን ዕድሜ እና የአከባቢውን ጥራት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚቀሩትን ዛፎች ብዛት በሚወስኑት ጥግግት ቻርቶች መሠረት ነው ። አንዳንዶቹ ዛፎች ተመርጠው ስለሚወገዱ ለዛፎች እድገት የሚያስፈልገው መደበኛው የጥግግት መጠን እደተጠበቀ ይቆያል። የተመረጡ ዛፎችን በማስወገድ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የደን ርጋፊ/ፍቅፋቂ ክምቸትን በመከላከል በቂ የሆነ ከፍተኛ መጠን ያለው ጥላ ማግኘት ይቻላል።

መግረዝ - መግረዝ ከመሬት ቢበዛ 2.5 ሜትር፥ የዛፉን የታችኛውን ቅርንጫፎች እስከ ቁመቱ አንድ ሦስተኛው መቁረጥን ያካትታል። የእሳት አደጋ ከፍተኛ በሆነበነባቸው በመዝናኛ ቦታዎች እና በመንገዶች ላይ መግረዝ እስከ 4 ሜትር ሊደርስ ይችላል። ይህ የዛፉ የታችኛውን ቅርንጫፎች በማስወገድ የዛፉ ጫፍ ከመሬት ጋር እዳይገናኝ ለማድረግ ነው። የታችኛው ቅርንጫፎች በጣም ደረቅ ስለሚሆኑ እሳት በተነሳ ጊዜ ወደ ላይኛው የዛፍ ክፍል ያስተላልፍሉ። በመግረዝ ሂደት ውስጥ በዛፎች ላይ እስከ ዛፉ ጫፍ ድረስ እሳት ሊያስተላልፉ የሚችሉ የሐረግ ተክሎችም ይወገዳሉ

የተቆረጡ ዛፎችን እና ቆሻሻዎችን ማስወገድ -የተቆራረጡ ዛፎች እና የደን ቆሻሻዎች ከደኑ ወደ መንገዱ ዳር ይጓጓዛሉ። ከዚያም ተቆርጠው ከደን ከወጡ በኋላ ለተለያዩ አገልግሎቶች ይውላሉ ወይም ደግሞ መሬት ላይ ይበተናሉ።
ኬ ኬ ኤል ጄ ኤን ኤፍ በመንገዶቹ ዳር ቢያንስ 30 ሜትር ርቀት ላይ ያለውን የደን መስመር ከዛፍ ቁርጥራጮች እና ቆሻሻዎች ነፃ ለማድረግ ጥበቃ ያደርጋል። በተጨማሪም በአቅራቢያው ያሉ ማህበረሰቦች እና ነዋሪዎቸ የተቆረጡ ዛፎችን እና የዛፍ ቆሻሻን ለማሞቂያ እና ለሌሎች አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ያበረታታል።

ቁርጥራጮቹን ማቃጠል - ይህ ለቁጥቋጦዎች አያያዝ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው የበይነገጽ ክዋኔ ነው። በተጨማሪም በተለያዩ በደን የተሸፈኑ አገሮች እንደ መደበኛ እና የተለመደ ስራ ነው።
ከደን ንጽህና ፥ የተመረጡ ዛፎችን ከማስወገድ እና ዛፎች ከተገረዙ በኋላ በደኑ በገደል ዳገት ላይ ወይም ከመንገድ ርቆ በሚገኝባቸው ቦታዎች አካባቢ ቁርጥራጮቹ ይቃጠላሉ።
የተመረጡ ቦታዎች ላይ የሚደረግ ስራ ለምሳሌ አንድ ዛፍ መቁረጥ ያሉ ስራዎች ቁርጥታጮችን መገንጠል እና ማቃጠልን አያበረታቱም።
ከደን ቃጠሎ በኋላ የተቃጠለ መኪና። ፎቶ: ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፎቶ ማህደር
እንዲሁም፣ በእሳት አደጋ ጊዜ ፈጣን እና ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት፣ ኬ ኬ ኤል ጄ ኤን ኤፍ ለሚከተለው የማረጋገጫ ዝርዝር ተጠያቂ ነው።

ውሃ - በእሳት አደጋ ጊዜ የእሳት አደጋ መኪናዎችን እና የእሳት አደጋ ተከላካዮችን ውሃ ለማቅረብ የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት መስራት። እሳትን ለማጥፋት ውሃ በጣም አስፈላጊው የሎጂስቲክስ ክፍል ነው።

የመመልከቻ ማማዎች - እነዚህ የመመልከቻ ማማዎች የደን ቃጠሎን አስቀድሞ ለማወቅ እና የእሳት አደጋ ተከላካዮችን ወደ ቦታው ለመምራት የታቀዱ ናቸው። የመመልከቻ ማማዎቹ በኔትወርክ ውስጥ የተቀመጡ ሲሆን ይህመ ከደኑ በላይ የሚወጣው ጭስ ቢያንስ ከሁለት ማማዎች ላይ ለማየት ያስችላል። ይህም የእሳቱ መነሻ ቦታ በትክክል ለማወቅ ያስችላል። የጥበቃ ማማዎቹ ቢያንስ 12 ሜትር ከፍታ አላቸው።

ምልክት ማድረግ - የመድረሻ ምልክቶች እና የአቅጣጫ ምልክቶች በደን ቃጠሎ ጊዜ ትክክለኛ የመሰብሰቢያ ቦታዎችን በፍጥነት ለማግኘት ይጠቅማሉ። በደን መንገዶች ላይ ያሉት የደን እሳት አቅጣጫ ምልክቶች በሕዝብ ሥራዎች ዲፓርትመንት (ዲ ፒ ደብሊው) የተወሰነውን የመንገድ ቁጥር እንዲሁም ስለ ፎር ዊል ድራይቭ (ኤ ቲ ቪ) ገደቦች እና የተዘጉ መንገዶች ማስጠንቀቂያዎች ያካትታሉ። የደን ቃጠሎ መድረሻ ምልክቶች የተከሰተ የደን እሳት እየጠፋ በነበረበት ወቅት ‘ወደ እሳቱ’ የሚል ተንቀሳቃሸ ምልክቶች ናቸው። የእሳት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ እነዚህ ምልክቶች በደን ውስጥ የሚቀመጡት የእሳት አደጋ መከላከያ ኃይሎች ዋና ዋና መንገዶችን በመተው በቀጥታ ወደ እሳቱ የሚወስዱ መንገዶችን እንዲከተሉ ለመምራት ነው።

*በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ያለው መረጃ የተወሰደው በ ኬኬኤል -ጄ ኤንኤፍ ባለሙያ ሰራተኞች ከተጻፈው የደን ንድፈ-ሐሳብ ከተባለው መጽሐፍ ነው።
ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የእሳት አደጋ መኪና። ፎቶ: ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፎቶ ማህደር