ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ ፣ በመሬት ልማት ባለስልጣኑ በኩል፣ በ1961 ከመንግስት ጋር በገባው ቃል ኪዳን መሰረት የእስራኤል ህጋዊ የሆነ የደን አስተዳደር ነው። የኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ የደን ልማት ፖሊሲ ዛሬ እና ወደፊት ሁሉንም የእስራኤል ዜጎች ለማገልገል የተነደፈ እና በዘላቂ ልማት መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ነው።
ከነዚህ መርሆዎች ጋር በሚስማማ መልኩ የኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ የደን አስተዳደር የሚከተሉትን ያጠቃልላል
- ከተፈጥሮ ስነ-ምህዳር ጋር የሚጣጣም እና ስነ-ምህዳራዊ የማይጻረር አካሄድ።
- ደን ህዝብን እና ማህበረሰቡን የሚያገለግልበት ማህበረሰባዊ አስተሳሰብ።
- የቱሪዝም ልማትን፣ የግጦሽ እርባታን፣ የእንጨት ኢንዱስትሪዎችን ወዘተ የሚያካትቱ ኢኮኖሚያዊ አጠቃቀሞችን እና ውጥኖችን ማስተዋወቅ።
- ከትውልድ-ትውልድ እኩልነት መርህ ጋር በጠበቀ መልኩ ደኖችን በነጻ ለህዝብ ክፍት ማድረግ።
- የእስራኤላውያን ጫካዎች ስፋት እና ጥራታቸው ለወደፊት ትውልዶች ከመጨነቅ አንጻር መጠበቅ።
ኬ ኬ ኤል-ጄ ኤን ኤፍ እስራኤል በደን ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የፈራረመችባቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለምሳሌ እንደ አጀንዳ 21 እንዲሁም ፀረ-በረሃማነትን፣ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ እና ሌሎችም ላይ በጆሃንስበርግ ኮንቬንሽን በተደነገገው እና የተፈረመውን የትግበራ ዕቅድ መሠረት ለመፈፀም ቁርጠኛ ነው።