የእስራኤል ግዛት በርካታ ፈንጂዎችን እንደያዘ ማወቅ ለእርስዎ አስፈላጊ ነው, ይህም ለጎብኚዎች አደጋን ያመጣል፡፡ ፈንጂዎች ከማህበረሰቦች፣ ከእርሻ መሬት ወይም ከታዋቂ የእግር ጉዞ መንገዶች ጋር አቅራቢያ ላይ ሊገኙ ይችላሉ። የታጠሩ እና በግልጽ ምልክት የተደረገባቸው ናቸው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ፈንጂዎች ከተከለሉት ፈንጂዎች አጠገብ ባሉ ቦታዎች ላይ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ባለፉት ዓመታት ፈንጂዎች አንዳንድ ጊዜ ከተከለሉት ቦታዎች ታጥበው ወደማይታወቅ ቦታ ይሄዳሉ። እንደዚህ አይነት ሰፋፊ መሬቶችን ማጠር የማይቻል በመሆኑ, እነዚህ ቦታዎች በታዋቂ ምልክቶች ብቻ የተሰየሙ ናቸው፤ ስለዚህ በውስጣቸው ያለው እንቅስቃሴ በተወሰነላችሁ መንገዶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው፡፡
እባክዎ የሚከተሉትን የደህንነት ማስጠንቀቂያዎችን ይመልከቱ
-
እየተራመዱ፣ ሳይክል እየነዱ ወይም የትኛውንም መኪና ሲጠቀሙ ለራስዎ ደህንነትና ከተፈጥሮ አንጻር እባክዎ የተመረጡመንገዶችን ብቻ ይጠቀሙ፡፡
-
በግልጽ ከተፈቀዱ ቦታዎች በስተቀር አጥሮችን አይዝለሉ፡፡ የታጠረ ቦታ አጋጥምዎታል? በፍጹም ወደ ውስጥ አይግቡ፡፡
-
በጉዟችሁ ላይ እንግዳ የሆነ፣ አጠራጣሪ ወይም ግልጽ ያልሆነ ነገር ካጋጠምዎ፤ በፍጹም አይንኩት፡፡ ምናልባት ከፈንጂዎች የቀረ ሊሆን ይችላልና፡፡
-
የተሳሳተ መንገድ ከመረጡ እና ፈንጂ ወዳለበት ወደሚጠረጠር አካባቢ ከገቡ፤ እዛው ይቁሙና የጥበቃ አካላትን ወይም ፖሊሶችን ደውለው ይጥሩ፡፡
-
የሚጠረጠሩ ቦታዎችን እንዴት መለየት ይቻላል; በአጥር የታጠረና በቢጫ ቀለም መደብ ላይ ቀይ የሶስት ማዕዘን ምልክት ያለበት ነው፡፡
-
ፈንጂ በሚገኝበት ቦታ ላይ የሚገኙ የስነምግባር ደንቦች በእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ማዕድን ማስወገድ ባለስልጣን የቀረቡ ናቸው።