የጽዮናውያን አመራር አካዳሚ (ዚ.ኤል.ኤ)

የጽዮናውያን አመራር አካዳሚ (ዚ.ኤል.ኤ) በከረን ካያመት ለእስራኤል-የአይሁድ ብሔራዊ ፈንድ (ኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ) እና የዓለም የጽዮናውያን ድርጅት (ደብልዩ.ዚ.ኦ) የሚመራ የጋራ እንቅስቃሴ ሲሆን የወደፊት የጽዮናውያን አመራርን እና አዳዲስ ከመላው ዓለም የመጡ የጽዮናዊት ድርጅት ደጋፊ ትውልዶችን የማስተዋወቅ አስፈላጊነት ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ ነው።
የዚህ ፕሮግራም አላማ በአለም ዙሪያ ካሉ የአይሁድ ማህበረሰቦች የተውጣጡ፣ ለእስራኤል መንግስት እና ለአይሁድ ህዝብ ደህንነት የሚተጉ የተመረጡ ወጣት መሪዎችን ማዳበር እና ማጎልበት እና በተለየም መልኩ ኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ ገንዘብ ለማሰባሰብ ነው።

የዚ.ኤል.ኤ አባላት በኖቤል ተሸላሚዎች፣ በመንግስት መሪዎች፣ በህዝብ ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የKKL-JNF ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የጽዮናውያን አክቲቪስቶች እና መሪዎች እና ሌሎች ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች በመሳሰሉ ሊቆች የሚሰጥ በድርጊት የተሞላ፣ ትምህርቶችን እና አውደ ጥናቶች ያካተተ ትርጉም ያለው ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋሉ።
ፕሮግራሙ በ5 አንኳር ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የተደራጀ ነው፤ ዲፕሎማሲ እና ሀስባራ; ጽዮናዊነት, ይሁዲነት እና የእስራኤል ወቅታዊ ጉዳዮች; የአመራር ስልጠና; የገንዘብ ማሰባሰብ እና የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች; እና ኢኮሎጂ, አካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ።

በየአመቱ አንድ ዙር የዚ.ኤል.ኤ ፕሮግራም እናካሂዳለን። ዘንድሮ 2024 ሶስተኛችን ይሆናል። ፕሮግራሙ በ10 ወራት ውስጥ በየሁለት ሳምንቱ የዙም ምናባዊ ስብሰባዎችን እና ሁለት አለምአቀፍ በአካል ያሉ ኮንፈረንሶችን ያካትታል።
 
 
The Zionist Leadership Academy (ZLA)