ይህ ከኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ዋና ፕሮጄክቶች አንዱ ሲሆን በእስራኤል ውስጥ በማዕከሉ እና በአከባቢው መካከል ክፍተቶችን ለመዝጋት እና ለእስራኤላውያን ለእያንዳንዱ ተማሪ እኩል እድሎችን ለመስጠት ያለመ ነው። እንደ የፕሮጀክቱ አካል፣ በተመረጡ የእስራኤል ዳር ከተሞች ዘጠኝ አዳዲስ የቅርስ ማዕከላት ተገንብተዋል። የኦፋኪም ቅርስ ማእከል የተለገሰው በኬኬኤል-ፈረንሳይ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የትምህርት ክፍል ስራ አስኪያጅ ሳር ሻሎም ገርቢ፣ የ ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የደቡብ ክልል ስራ አስኪያጅ ያኒቭ ማይሞን እና የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ የፈረንሳይ ዋና ተላላኪ ዳንኤል ቤንሉሉ ተገኝተዋል።
በማዕከሉ ውስጥ ያለው ሁለገብ እንቅስቃሴ በእስራኤል ጂኦግራፊ እና ታሪክ ፣ ስልጣን ፣ አመራር ፣ ዘላቂነት ፣ ሀገር ግንባታ እና ሌሎችም ብዙ ትምህርቶችን ያጠቃልላል። ማዕከላቱ የወጣቱን ማህበረሰብ የጽዮናዊ እሴቶችን እንዲለዩ፣ በውትድርና ወይም በብሔራዊ አገልግሎታቸው ጊዜ ትርጉም ያለው ሚና እንዲጫወቱ እና የአካዳሚክ ጥናቶችን እንዲሞክሩ ያበረታታሉ። በተጨማሪም ማዕከላቱ ንግግሮችን እና የሚያበለጽጉ ተግባራትን በማካሄድ እና ተግባራቸውን ወደ አዲስ ደረጃ ለማድረስ ለወጣቶች እንቅስቃሴ አማራጭ ይሰጣሉ።
የ ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ሊቀመንበር ኢፋት ኦቫዲያ-ሉስኪ፣ "ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ በኔጌቭ እድገት ውስጥ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታል፤ በጽዮናውያን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮችም መካከል አንዱ ነው።ዛሬ የማዕዘን ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓቱን ልናከብር በዚህ የተገናየንበትን የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ቅርስ ቤትም የዚሁ አንዱ አካል እንደሆነ እና በከተማው ውስጥ ካደረግናቸው በርካታ የድጋፍ ተግባራት መካከል እንደሆነ እመለከታለሁ።”
"ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ በኦፋኪም ውስጥ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ ሚሊዮኖችን አፍስሷል። ይሄ የተነቃቃ ጽዮኒዝም፣ ግልጽ እና ቀላል ነው። ራእዩን እውን እናደርጋለን፣ በረሃው እንዲያበቅል እናደርጋለን፣ እስራኤልን ከአይሁድ ዲያስፖራ ጋር እናገናኛለን፣ እናም ህልሞችን ወደ እውነት እንለውጣለን። የደቡብ እስራኤል ልማት ከፍተኛ ስልታዊ ጠቀሜታ አለው፣ እናም ይህን ሂደት በመምራታችን ኩራት ይሰማናል።”
ከንቲባ ኢትዝሃክ ዳኒኖ እንደተናገሩት፣ "ይህ ፕሮጀክት ለበርካታ አመታት ቢዘገይም ከሌሎች ከንቲባዎች የጋራ ትግል በኋላ ለመጀመር ችለናል። በኦፋኪም የሚገኘው የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ቤት ለወጣቶች መደበኛ ያልሆነ ትምህርት የሚያስተዋውቅ ሲሆን የትምህርት ድጋፍ የሚያገኙ፣ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር የተጣጣሙ ትምህርቶችን የሚያገኙበት፣ ጊዜያቸውን በዘመናዊ ግቢ ውስጥ የሚያሳልፉበት እድል ይኖራቸዋል፤ ከሁሉም በላይ - የአካባቢውን ወጣቶች አመራር ያዳብራሉ።”
"እነሆ፣ መጪው ትውልድ እሴቶችን እንዲሁም የላቀ ደረጃን ይማራል፣ ይመኛል፣ በዚህ ቦታ ታዋቂው የአይሁድ አስተሳሰብ - የእስራኤል እጅግ አስፈላጊ ሃብት - ያድጋል። ዛሬ ለቀጣዩ ትውልድ ለተሻለ ጊዜ ጠንካራ እና የበለጸገ ማህበረሰብ የምንገነባበትን ዘር ዘርተናል እናም የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠናል ። ኬኬኤል-ጄኤንኤፍ እና ኬኬኤል ፈረንሳይ ለአገር ልማት ላሳዩት የማይናወጥ ራዕይ እና በኦፋኪም የሚገኘውን የኬኬኤል-ጄኤንኤፍ ቅርስ ቤት ለማቋቋም ላደረጉት እገዛ እናመሰግናለን።”