"ሰላምታ እናቀርብላችኋለን"፡ ኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ በኦክቶበር 7 ህይዎትን ያተረፉ 20 መሪ ሴቶች በተገኙበት ስነ ስርዓት ላይ 'ሄሮዊንስ መንገድን (የሴት ጀግኖች መንገድን)' በኦፋኪም ፓርክ አስመረቀ።

በብረት ሰይፎች ሂደት ወቅት የኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ እንቅስቃሴ።
በአሰቃቂ ጥቃ ህይወትን ላዳኑ ጀግኖች እስራኤላውያን ሴቶች መታሰቢያነት የተዝጋጀው መንገድ እሁድ ጥር 7 ቀን ተመርቋል።
ታሪካቸውን በኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ ድህረ ገጽ ላይ ለመለጠፍ ፍላጎት ያላቸው ሴቶች tamarl@kkl.org.il ላይ ኢሜይል ሊልኩልን ይችላሉ
የኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ ሊቀመንበር ኢፋት ኦቫዲያ-ሉስኪ: "መመልከት የቻለ ማንኛውም ሰው በጥቅምት 7 ቀን በራሳቸው ተነሳሽነት የቆሙትን ሴቶች ጨምሮ ብዙ ሴቶች ጀግንነትን በተግባር አሳይተዋል። ዛሬ እነዚህን ሴቶች ለማክበር መጥተናል። የደህንነት በሮች እደተዘጉ ለመጠበቅ የተዋጉት፣ ደፋር የደህንነት አስተባባሪዎች ፣ ታጋዮች ፣ ፖሊሶች ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያዳኑ ሐኪሞችና ህክምና ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች።ለፍርሃት እጃቸውን ያልሰጡ ፣ ለማረፍ ያልቆሙ ፣ ድፍረትን ያሳዩ እና ያለማመንታት የተንቀሳቀሱ ። እያንዳንዷ የራሷን ልዕለ ኃያል ያላት። ሥጋና ደም የጽዮናውያን ጀግኖች እዚሁ ከእኛ ጋር የቆሙትን ጀግኖች። በተለየ መንገድ የክብር ሰላምታ እንሰጣለን። እዚህ ሐውልት ወይም ድንጋይ አላስቀመጥንም፤ መንገድን ጠርገናል፣ አስጠርግተናል፤ ምክንያቱም የጥቅምት 7 ጀግኖች ከኛ አስቀድሞ የጀምለና ከእኛ በኋላም የሚቀጥል ረጅም መንገድ አካል ናቸውና።
በሊኖር አባርጊል አስተባባሪነት የተዘጋጀው ልዩ ዝግጅት በበዓሉ ላይ የተገኙ 20 ሴቶችን ጀግንነት አክብሯል።
የዛካበጎፈቃደኛኑሪትኮኸን: "እኔ እና በዛካ ውስጥ ያሉ ባልደረቦቼ በጋዛ ኤንቨሎፕ ላይ ኖረን አስከሬኖቹን ሰበሰብን እያንዳንዱ የደም ዱካ, በመሬት ውስጥ ያለው ቀዳዳ ሁሉ, የተኩስ ታሪክ, የእጅ ቦምብ ፍንዳታን ታሪክ ይናገራሉ። ቀን እና ሌሊት ሁሉንም አካላት እና ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ ሰርተናል።  በሴትነት በመወለድ በብሔራዊ ትንሳኤ በመትከል ግንኙነተ ይታየኛል - ጠንካራ መሆን እና ተስፋ ለመቁረጥን ምክንያቱም ለመቆየት ነው እዚህ ያለነው
 
ሱፐርኢንቴንደንት ሞራን ቴድጊ፡ "የእስራኤል የፖሊስ መኮንኖች በዚያ አስፈሪ ቅዳሜ የመከላከያ ጋሻ ሰተው ነበረ። ራሴን ሙሉ በሙሉ ለሥራው ማዋል ያለብኝ ቅጽበት መሆኑን ተገነዘብኩኝ። እስካሁን መስማት ከምችለው ቦምብ ፍንዳታ እና በተተኮሱ አር.ፒ.ጂ ሮኬቶች መካከል አንድ ነገር አውቅ ነበር፡ እነሱ እንዳያመልጡ ብለን ህይወታችንን ለአደጋ እናጋልጣለን። የኦፋኪምን ከተማ እንጠብቃለን፡ የተሻለ የሰላም እና የደህንነት ቀናትን እንድናይ ይሁንልን።
 
ታሊ ሃዳድ፡ "ልጄ ኢታማር አላማው ቤቱንና አገሩን መጠበቅ እንደሆነ ስላወቀ ለውጊያ ወጣ፡፡ መሳሪያውን ይዞ ወደ ተኩስ ድምጽ ሄደ። ምንም ቢሆን ልጄ ስለሆነ ተከተልኩት። የኃይለኛ የውጊያ ድምጽ ሰምተን የአሸባሪዎች ኮንቮይ ሲዘምት አየን። የሞተቱትን የቆሰሉትን አይቼ ወደ ቤቴ ሮጬ መኪናውን ይዤ የቆሰሉትን ለማንሳት ወሰንኩ። የመጀመርያው የቆሰለው የኔ ኢታማር ነው። እሱን ወስጄ ከእርሱ ጋር ወደ ሆስፒታል እንደማልሄድ ነገርኩት ወደተጎዱተን ወደብዝሃኑ መመለስ ስለነበረብኝ። 12 ተጨማሪ የቆሰሉ ሰዎችን አነሳሁ። ኢታማር በአራት ጥይት ተመቶ ቢሆንም በሕይወት ተመለሰ። የእስራኤል ሕዝብ ለዘላለም ይኑር!"