አዲስን ሕይወት ማሳደግ፡ የኖቫ ፌስቲቫል የተጎጂዎች ቤተሰቦች የሚወዷቸውን ያጡበት ስፍራ ላይ ዛፎችን ተክለዋል

በብረት ሰይፎች ሂደት ወቅት የኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ እንቅስቃሴ።
መጪውን የቱ ቢሽቫት በዓል በመጠባበቅ፣ ..ኤል-.ኤን.ኤፍ በኖቫ ፌስቲቫል እልቂት ዘመዶቻቸውን ካጡ ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር ልዩ የሆነ የተክል የመትከል ቀን በሪም መዝናኛ ስፍራ አዘጋጅቷል። ከኬ..ኤል-.ኤን.ኤፍ ለዪ የእስራኤል ኤንቨሎፕን ለመገንባት እንቅስቃሴ አካል አንዱ፣ የተቃጠለው ግቢ እንደገና አረንጓዴ ለማድረግ በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ዛፎች 364 የፓርቲ ተሳታፊዎች መታሰቢያነት ተክለዋል።

ከዝግጅቱ ተሳታፊዎች መካከል በጋዛ ታግተው የተገደሉት የሻኒ ሉክ እናት ሪካርዳ ሉክ ይገኙበታል። በግብዣው ላይ የተገደለው የማፓል አደም እናት ዮና አደም። ዮራም ዩዳይ፣ በኮንቴይነር ውስጥ ተደብቆ በኖቫ በተካሄደው ድግስ ላይ የተገደለው የሮን ዩዳይ አባት። በሪም ድግስ ላይ የተገደለችው የማኦር ግራትዚያኒ እህት ሳሮን ግራትዚያኒ።
ቅዳሜ ኦክቶበር 7 ቀን 6፡22 ላይ በበዓሉ ግቢ ውስጥ የሲሪን ድምጽ ተሰምቷል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ፓርቲው እንዲዘጋ ተወስኖ የፖሊስ አባላት ህዝቡን ማባረር ጀመሩ። በዚሁ ጊዜ አሸባሪዎች የእስራኤልን ግዛት መውረር ጀመሩ። አሸባሪዎቹ ፒክአፕ መኪና እና ፓራግላይደር ተጠቅመው ወደ ግቢው በመድረስ የፓርቲውን እንግዶች ላይ በጠመንጃ እና በአርፒጂ መተኮስ እና የእጅ ቦንብ መወርወር ጀመሩ። አሸባሪዎቹ ብዙ የፓርቲውን እንግዶች ገድለው ሟች ፍተሻ በማድረግ ግቢው ተቃጥሏል። ኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ አሁን ግቢውን እና መላውን የእስራኤል ኤንቨሎፕ እንደገና ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።

የኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ ሊቀመንበር ኢፋት ኦቫዲያ-ሉስኪ፡ "ኦክቶበር 7 ቀን እስራኤል እጅግ በጣም ጨለማ የሆነ ቀን አሳልፋለች።  የሪም መዝናኛ ስፍራ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በየዓመቱ የሚመጡበት የነበረ ቦታ የአሰቃቂ እልቂት ቦታ ሆነ። የተጎጂ ቤተሰቦች ስቃይ የመላው የእስራኤል ህዝብ ስቃይ ነው እኛም ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረን እንቆማለን።  የእስራኤል ህዝብ ታሪክ የሰቆቃ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የመነቃቃት ታሪክም ጭምር ነው። በዚህ ቱ ቢሽዋት ዝግጅት የመልሶ ግንባታ እና የማደግ መልእክት እናመጣለን - ከአመድ ተነስተን በሬኢም እና በመላው እስራኤል ማህደር ውስጥ አዲስ ሕይወት እናሳድጋለን። በእያንዳንዱ ትውልድ እኛን ለማጥፋት ይነሳሉ  እኛም ዳግም አገግመን እና አዲስ ሕይወት እናሳድጋለን። በዚህ ጊዜም ሁሉም ከኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍሰራተኞች  ለዚህ አገራዊ ተልዕኮ ተመልምለዋል፣  ኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ እዚህ እንደገና ሕይወትን ለመገንባት ግንባር ቀደም ይቆማል። አንድ ላይ ሆነን እናሸንፋለን።”
ሜይራቭ እና ዶሮን ማዳር ለልጃቸው ለ26 ዓመቱ ሻህ ዮሴፍ ማዳር መታሰቢያ ዛፍ ለመትከል የመጡት “ሻሃክ አምስት ወንድሞች ነበሩት እና በቤን ጉሪዮን የሆቴል አስተዳደር እና ቱሪዝም ተማሪ በትምህርቱ የላቀ ውጤት ያስመዘገበ ዩንቨርስቲ ተማሪ እና በነሃል ብርጌድ ታጋይ ነበር” ብለው ተናግረዋል። ዛሬ እዚህ የመጣነው እሱን የሚዘክር እንደ ሻህክ የሚነሳና የሚበቅል ፣በፍቅር ፣በብርሃን እና በደስታ የተሞላ ዛፍ ለመትከል ነው።

 ጠንካራና የሚያድግ እንዲሆን ፣ ሥሩን ወደ አፈር ውስጥ እየሰደደ ለማየት እንመኛለን።  ከአስራ ሁለት ዓመታት በፊት ፣ የዶሮን እህት ሁለት ልጆችን በማደጎ ለማሳደግ ከተቀበልን ጊዜ ጀምሮ የአናሞኒ ቡድን አባል ነን። ሁሉም ነገር የተገናህኘ ነው።

ልጁ ራም በኖቫ በተካሄደው ግብዣ ላይ የተገደለው ኑሪት ሻሎም "ራም የምወደው ልጄ በኦክቶበር 7 በግብዛው ውስጥ ተገድሏል.   ህይወትን, ሁሉንም ሰዎች ይወድ ነበር, እና ሁልጊዜም ፈገግ ያለ ልጅ ነበረ። ከዝግጅቱ ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ከዩናይትድ ስቴትስ የተመልስነው እና በአሜሪካ እያለን ኖቫ ተብሎ በሚጠራው ዝግጅት ውስጥ እንደነበረ እና በእስራኤል ውስጥ እንደዚህ ያለ ዝግጅት እንዳለ እና ወደዚያ ዝግጅት እንደሚሄድ የነገረኝ ቢሆንም ግን ከዚያ ተመልሶ አልመጣም። ዛሬ ወደ ተከላ የመጣሁት ለእሱ መታሰቢያ ባህር ዛፍ ለመትከል ነው። ይህ በኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ በኩል የተደረገው በጣም ልብ የሚነካ እንባ የሚያስመጣ ተግባር ነው። ኬ.ኬ.ኤል-ጄ.ኤን.ኤፍ ላደረጉት አስደናቂ ተነሳሽነት እና መታሰቢያ ፕሮግራም ለማመስገን ቃላት ያጥረኛል።